There are 2,185 self-help development groups with 36,509 members engaged in various activities organized by the Terepeza Development

Association in the districts of Walaita Zone; among them 352 of these self-help groups located in Abala Abaya district.

The “Tinsae” self-help group from Abala Gafata Kebele, Abala Abaya District, started their work by saving two Birr a week, then increased it to five Birr, then ten Birr, and strengthened their union and started their business by raising sheep and goats.

Next, they aggregate grain and sold it for a while to improve their profit. Now, realizing that it is important in order to their area; they bought a tent to use for various social and religious ceremonies and plan to earn income by renting it.

The members of the self-help group say "work hard and save together to grow together" stated that they believe that they can grow more by working hard in the future.

TDA believes self-help groups as the best development approach; by adapting profitable and market-oriented new and existing local crop production and creating market linkages.

As well as by creating a favorable environment for our community to learn and collaborate each other, it is known that it is a very profitable method to introduce development activities to the society that can change the life of our community in a short time.

Thank you, all our partners' for working with us!

Serving the whole person!

===================

በጠረጴዛ ልማት ማህበር ተደራጅተው በተለያዩ ስራዎች የተሰማሩ 36,509 አባላትን ያቀፉ 2,185 የራስ አገዝ ልማት ቡድኖች በወላይታ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች ሲኖሩ ከእነዚህ ውስጥ 352 የራስ አገዝ ቡድኖች የሚገኙት በአባላ አባያ ወረዳ ነው።

ከሰሞኑ አባላ አባያ ወረዳ አባላ ጋፋታ ቀበሌ የሚገኘው "ትንሳኤ" የራስ አገዝ ቡድን በሳምንት ሁለት ብር በመቆጠብ ስራቸውን በመጀመር ቀጥሎም ወደ አምስት ብር ከዛም አስር ብር በማሳደግ ህብረታቸውን በማጠናከር የንግድ ስራቸውን በግና ፍየል በማሞከት ጀመሩ።

ቀጥለውም እህል አሰባስበው ለጥቂት ግዜ አዘግይተው በመሸጥ ትርፋቸውን በማሳደግ አሁን በአካባቢያቸው አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት ለተለያዩ ማህበራዊና ሐይማኖታዊ ስነስርዓቶች የሚውል ድንኳን ገዝተው በማከራየት ገቢ ለማግኘት አቅደው በ173,000.00 ብር ድንኳን በማሰራት የተሰጣቸውን የስራ ፈጠራ ክህሎት በመጠቀም ወደ አዲስ ስራ ገብተዋል።

“አብሮ ለማደግ አብሮ መትጋትና መቆጠብ” መርሃችን ነው የሚሉት የማህበሩ አባላት ወደፊትም በትጋት በመስራት የበለጠ ማደግ እንደሚችሉ እምነታቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ልማት ማህበሩ የራስ አገዝ ቡድንን ተጠቅሞ አዳዲስ የአስተራረስ ዘዴዎችን፤ አዋጪና ገበያ ተኮር አዲስና ነባር የአዝርዕት አይነቶች በማላመድና የገበያ ትስስር በመፍጠር እንዲሁም አንዱ ከሌላው በቀላሉ ለመማማር እና ለመያያዝ ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የማህበረሰባችንን ሕይወት በአጭር ጊዜ ሊቀይሩ የሚችሉ የልማት ተግባራትን ወደ ህብረተሰቡ ለማስረጽ እጅግ ምቹ አሰራር በመሆኑ ላልፉት ሁለት አስርት ዓመታት ጀምሮ ሲሰራ በመቆየቱ እና ይበል የሚያሰኙ ለውጦችን ለማስመዝገቡ ተጠቃሚዎች ህያው ምስክሮች ናቸው።
ሁሉንም ያለልዩነት እናገለግላለን!